Questions & Answers About the Survey (Amharic)

ስለጥናት ዳሰሳው ጥያቄዎች እና መልሶች

ለጥያቄው የመለስኩትን ምላሽ ት/ቤቱ ያውቃል?
የጥናት ዳሰሳው እንደ የ CPS ወላጅ፣ አሳዳጊ ወይም እንክብካቤ ሰጪ ስላለዎት ተሞክሮ ይጠይቃል - መልሶችዎ በማን እንደተሰጡ አይታወቅም፡፡ የትኛው መልስ በማን እንደተሰጠ የምናውቅበት መንገድ የለም፡፡ በጥናት ዳሰሳ ላይ ከሚሰጡ አስተያየቶች ት/ቤቶች ብዙ ነገር ይማራሉ - ለምሳሌ የእርስዎ ቤተሰብ የተማሪ የመማር ሂደትን እንዲያግዝ ት/ቤቱ ሊረዳ ስለሚችልበት መንገድ ያለዎትን ሀሳብ እና ት/ቤቱ ለሁሉም ቤተሰቦች ምቹ እንደሆነ/እንዳልሆነ እንደሚያስቡ፡፡

ይህ የጥናት ዳሰሳ በ CPS እንዴት ግልጋሎት ላይ ይውላል?

እንደ አጠቃላይ የአውራጃው እቅድ ሂደት የቤተሰብ የጥናት ዳሰሳው ለተማሪዎች የተሻለ ውጤት ላይ በማተኮር የመማር፣ የመሞከር፣ የማጣራት እና የመገንባት ቀጣይ ኡደት አካል ነው፡፡

CPS ትምህርት የሚያገኝበት መንገዶች እና የምንማራቸው ነገሮች ምላሽ ምሳሌዎት የሚከተሉትን ያካትታሉ፡

  • የጥናት ዳሰሳውን በሞሉ ቤተሰቦች የተገለጸ ችግርን ለመፍታት የሚያስችል የበለጠ ምንጮችን ማዘጋጀት
  • በጥናት ዳሰሳው ላይ በተነሳ አንድ ርዕስ ዙሪያ ስልጠና እና ሙያዊ ማስተማርን ማስቀደም
  • አዲስ የወላጅ የትምህርት መጽሀፍ ወይም ወርክሾፕ መፍጠር
  • ከጥናት ዳሰሳው የተገኘ የመጀመሪያ ደረጃ ግኝትን የበለጠ ለመመርመር የቡድን ጥያቄዎች ማዘጋጀት

በትምህርት ቤቱ ከአንድ በላይ ልጅ ካለኝ፥ ጥናቱን ስንት ግዜ መመለስ ይኖርብኛል?
በአንድ ቤተሰብና በአንድ ትምህርት ቤት አንድ ግዜ ጥናቱን እንዲመልሱ አንጠይቃለን። የምላሽ ዉጤታችንን በትምህርት ቤቱ ባሉ የቤተሰቦች ቁጥር ብዛት እንለካለን (በተማሪዎች ቁጥር አይደለም)። ልጆች በሁለት ወይም ከዛ በላይ ባሉ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች ካልዎት፥ እባክዎን ለእያንዳንዱ ትምህርት ቤት ጥናቱን ይመልሱ፥ ጊዜ ካልዎት። “ስለ ልጅዎና ቤተሰብዎ” የሚለው ክፍል ዉስጥ፥ ምላሹን ትልቁን/ቋን ልጅ በማሰብ ይመልሱ ዘንድ እናሳስባለን።

ስለ ልጄና ቤተሰቤ መሰረት ለምንድን ነው ጥያቄዎች የምትጠይቁት?
Cambridge Public Schools (የኬምብሪጅ የህዝብ ትምህርት ቤቶች) ሁሉም ተማሪዎችና ቤተሰቦች በትምህርት ቤቶቻችን አዎንታዊ ልምዶች እንዲኖራቸው ለማድረግ የተሰጠ ነው። ስለ መሰረትዎ መረጃ በመስጠት፥ የተማሪው ቆዳ ቀለም፥ ዝርያ፥ ፆታ፥ የፆታ ዝንባሌ፥ ቤት ዉስጥ የሚነገር ቋንቋ ወይም የነፃ/ቅናሽ ምሳ ሁኔታ በCPS ዉስጥ ማንኛዉም አይነት ተፅኖ ካላቸው እንዴት አይነት አዎንታዊ ተሞክሮ እንደሚኖራቸው ማየት ያስችለናል።

ያለፉት ጥናቶች ያሳዩት በትምህርት ቤቶቻችን ራሳቸዉን ከሁለት ጾታዎች አንዱ በሆነ መልክ በማይገልፁ ወይም ተላላፊ የፆታ ዝንባሌ እንዳላቸው የሚገልፁ የተማሪዎች ቤተሰቦች በይበልጥ አሉታዊ ተሞክሮ እንደነበራቸው ነው። ለዚህ መረጃ ምላሽ፥ CPS ለእነዚህ ተማሪዎችና ቤተሰቦች የትምህርት ቤቶቻችንን ምላሾች ለማሻሻል የተቀረፀ አዲስ ስልጠና መርሃግብር ፈጥሯል። እንዲህ አይነቶቹን ልዩነቶች በጣም በጥሞና በመውሰድና፥ ለሁሉም ቤተሰቦች ከፍተኛ እኩልነትና መካተት አርምጃ ለመውሰድ እንሰራለን።

በሙያዊ አገላለፅ፥ Panorama (ፓኖራማ) በጥቅሉ (በግኡዝ) ቁጥሮችን ማየት እንዲያስችል ወይም በተለያዩ የጥቅል ቡድኖች (ፆታ፥ የቆዳ ቀለምና/ዝርያ፥ የትምህርት ደረጃ፥ ወዘተ) የእኩልነት ጥያቄዎች የትምህርት ቤትን ገፅታ ሁኔታና የተማሪዉን ተሞክሮዎች እንዴት እንደሚነኩ እንድንረዳ ያግዘናል።

እንዴት ነው የስሜን ማንነት የምትጠብቁት?
ጥናቱ የሚካሄደው Panorama Education ( ፓኖራማ ኤዱኬሽን ) በሚባል የውጪ ድርጅት ነው። ቤተሰቦች ማንኛዉም ገላጭ መረጃ እንዲያካፍሉ አይጠየቁም፥ ከአንድ ስነ ሕዝባዊ ቡድን ውስጥ 10 ወይም ከዛ በላይ ግለሰቦች ለጥናቱ ምላሽ ከሰጡ ብቻ ነው ስለ ተለያዩ ስነ ህዝባዊ ቡድኖች መረጃ እንድናይ Panorama (ፓኖራማ) የሚፈቅድልን። Panorama (ፓኖራማ) የሚያሳየን የምንፈልገዉን የአንድ ስነ ህዝባዊ ቡድን የሁሉም አባላት አጠቃላይ መልሶችን ነው። ይህም የተናጠል ቤተሰብ በጥናቱ ላይ የሰጠዉን ምላሽ ማንኛዉም መረጃ ሳያሳይ የተሞክሮን ስርአት እንድንገነዘብ ይፈቅድልናል።

Website by SchoolMessenger Presence. © 2024 SchoolMessenger Corporation. All rights reserved.